መግቢያ፡ እንሰት (በሳይንሳዊ አጠራሩ ኢንሰቴ ቬንትሪኮሰም፤ የሙሳሴ ቤተሰብ) በአፍሪካ የሚገኝና በዚህ ወቅት ከ20 ሚሊዮን በላይ ለሚሆኑ የኢትዮጲያ ዜጎች በዋና የምግብ ሰብልነት እያገለገለ ያለ ተክል ነዉ፡፡ የዱር እንሰት በብዛት በምእራቡና ደቡባዊ የአፍሪካ ክፍል የሚበቅል ሆኖ፤ የእንሰት ጂነስ ከኤዢያ እስከቻይና የተሰራጨ ቢሆንም በገበሬዉ ማሳ የተላመደዉና የተተከለዉ በኢትዮጲያ ከፍታማ ቦታዎች ቢቻ ነዉ፡፡ በአነስተኛ ማሳዎች ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ የገበሬዉ ዝርያዎች (ፋርመርስ ቫራይቲስ) በተለያየ የአየር ፀባይና የስነምህዳር አይነቶች ተጠብቀዉ ይገኛሉ፡፡

የጥናቱስፋት፡ እንሰት ለምግብ ዋስትና እንዲዉል የሚደርጉት የተለያዩ ባህሪያት ያሉት ተክል ነዉ፡፡ ለመጥቀስም ያክል በተለያዩ አካባቢያዊ ሁኔታዎች ስር መብቀል መቻሉ፣ ድርቅን የመቋቋም ዝንባሌዉ፣ በአመት ዉስጥ በማንኛዉም ወቅት ምርቱ ተሰብስቦ ለምግብነት እና ለ ሌሎች አገልግሎት ሊዉል መቻሉ፣ በተጨማሪም ወሳኝ የሆነ የምግብ ሰታርች፣ የቃጫ፣ የባህል መድሃኒትና የከብት መኖ ምንጭ መሆኑ፣ ለባህላዊ ቤት የጣራ ክዳን መሆኑና የየተለያዩ ግብርና ዉጤቶችን መጠቅለያነት ማገልገሉ ተጠቃሽ ናቸዉ፡፡ አልፎ ተርፎም እንሰት የአፈርን አጠቃላይ የእርጥበትና ለምነት ሁኔታ ብሎም ማይክሮ ክላይሜት ሁኔታ የሚጠብቅ ሲሆን የተለያዩ ባህላዊና አካባቢያዊ ጥቅሞች ያሉት ነዉ፡፡ ከሌሎች በእንሰት ቤተሰብ ዉስጥ ከተካተቱ ዝርያዎች (ለምሳሌ የሙዝ ዝሪዎች) በአንጻራዊነት እንሰት ሰፊ ምርምር ያልተሰራበት ተክል ነው፡፡ በዚህች የምርምር ክለሳ ጽሁፍ በእንሰት ዙሪያ የተሰሩ የምርምር ስራዎችን መገማገም፣ ተጠንተዉ የሚገኙትን የእንሰት ጂኖምና ብዛዘር ሃብት መዘርዘር፣ በእንሰት በሽታ ዙሪያ ያለዉን እዉነታ ማሳየት፣ ብሎም ለእንሰት እጽዋት ልማት ሰፋፊ ጎዳናዎችን ማፈላለግ ይሆናል፡፡
ማጠቃለያ፡ እንሰት በበቂ ሁኔታ ያልተጠና የእስታሪች ምንጭነት ያለዉ ተክል ሲሆን በኢትዮጲያና በቀሩት ክፍለ አለማት ለተለያየ ጥቅም ሊዉል የሚችል እምቅ አቅም ያለዉ ተክል ነዉ፡፡ በተለያዩ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ የእንሰት ጥናት አናሳ ሲሆን ለመጥቀስም ያክል በተግባር የተፈተነ የወቅቱ የእንሰት አዘራርና አስተዳደደግ ፍቱንነት ጥናት፣ የገበሬ ዉዝርያዎች የዘረመል መሰረታዊ ተለያይነት ጥናት፣ ሳይንሳዊ ዘዴን የተከተለ የዝሪያ ድቅላ
ዘዴ ጥናት፣ እንትን የሚያጠቁ ወቅታዊና አዳዲስ መጤ በሽታዎችና ተባዮች ስነባህሪይ ጥናት፣ ለአዳዲስ አካባቢዎችና የመሬት አጠቃቀም ሁኔታዎች ያለዉ የመላመድ ሁኔታ፣ የአየሪ ንብረት ለዉጥ ወደፊት በእጽዋቱ ላይ ሚያመጣዉ ተጽእኖ ጥናት፣ የእንሰት የጫካ ዝርያዎች አጠባበቅ ሁኔታ፣ የእንሰት ተዋጽኦዎችና ተያያዠ ዉጤቶች እንዲሁም እስታሪች-ነክ ያልሆኑ ጥቅሞች፣ ብሎም ለእንሰት ምቹ የሆኑ የእድገትና የመራቢያ ስፍራዎች (ማይክሮ ባዮምስ) የመሳሰሉት ናቸዉ፡፡
ከዚህም በተጨማሪ በዚህ የክለሳ ጽሁፍ ላይ የእንሰት ሕያዉ ዝሪያ (ብዛዘር) ስብስብ ብሎም የዘር ባንክ (ሲድ ባንክ) አለመኖር፣ የእንሰት የመራቢያ ዘዴና የአበቃቀል ስርአት እዉቀት አለመኖር፣ ወደፊት ለሚደረግ የዝሪያ ማዳቀል ስራ ያለዉ የእዉቀት ክፍተት የሚገመገም ይሆናል፡፡ በዚህ ወቅት ያለዉን የተክሉን ጠቅላላ ነባራዊሁ ኔታዎች በመገምገም፣ እንሰትን አስመልክቶ የተሰሩ ጥናቶች ያሉባቸዉን ክፍተት ብሎም ምቹ አጋጣሚ በማሳየት የዚህን የተገለለና ለዘለቄታዊ እድገት የሚጠቅም እጽዋት ልማት ማሳለጥ እንደሚቻል ተስፋ እናደርጋለን፡፡